Posts

Showing posts from September, 2021
  የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከትግራይ ክልል ቀውስ ጋር በተገናኘ ተጨማሪ ማዕቀብ በኢትዮጵያ ላይ እንዲጣል አዘዙ 7/01/2014  የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከትግራይ ክልል ቀውስ ጋር በተገናኘ ተጠያቂ ባደረጓቸው የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስትና የአማራ ክልል ባለስልጣናት ላይ እንዲሁም በህወሓት እና በኤርትራ መንግስት አመራሮች ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል አዘዙ። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዛሬ በፈረሙት የስራ አስፈጻሚ አካል ትዕዛዝ የትግራይ ክልል ግጭት እንዲራዘም ፤ ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ እንዳይቀርብ ያስተጓጎሉ እና የቶክስ አቁም ስምምነት እንዳይደረስ እንቅፋት ሆነዋል ባሏቸው ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል ወስነዋል። ማዕቀቡ እንዲጣል ያዘዙትም ከላይ ለተጠቀሱት ጉዳዮች ተጠያቂ ናቸው በተባሉ የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የአማራ ክልል መስተዳደር ባለስልጣናት ላይ እንዲሁም በህወሓት እና በኤርትራ መንግስት አመራሮች ላይ እንደሆነ የአሜሪካ መንግስት ያወጣው መግለጫ ያመለክታል። ተጠያቂ ናቸው የተባሉት የመንግስት ባለስልጣናት እና የህወሓት አመራሮች ማንነት ግን ይፋ አልተደረገም። ይሁን እንጂ የአሜሪካ የመንግስት ግምጃቤት ከአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ጋር በመተባበር ተጠያቂ መሆን የሚገባቸውን እየለየ ማዕቀቡን ተግባራዊ የማድረግ ኃላፊነት ተሰጥቶታል። ማዕቀቡ በተመረጡ ግለሰቦች ላይ ብቻ ተግባራዊ እንደሚደረግ እና የኢትዮጵያ ህዝብን በማይጎዳ መልኩ እንደሚተገበር የአገሪቱ መንግስት ያወጣው መግለጫ ያመለክታል። ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ የጉዞ ማዕቀብ በኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት አመራሮች እና የህወሓት መሪዎች ላይ መጣሉ ይታወቃል። Sep. 17/2021 የዜናዉ ምንጭ Ethiopian Reporter ጋዜጣ ነዉ
 የጠ/ሚ አብይ አህመድ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት እንኳን ለ2014 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! ይሄን አዲስ ዓመት የምናከብረው በወሳኝ ሀገራዊ ፈተናና ተስፋ መካከል ሆነን ነው። ኢትዮጵያ በፈተና እና ተስፋ መካከል ሆና አዲስ ዓመት ስታከብር ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም። ምናልባትም የመጨረሻዋም አይሆንም። ኢትዮጵያውያን ፈተና የማያስበረግገን፣ ድልም የማያሰክረን ስለመሆናችን ዓለም ሁሉ ያውቃል። ፈተናን ወደ ዕድል በመቀየር ታሪክ ከሚያነሣቸው ሀገሮች ተርታ ለመሰለፍ ዐቅሙም አቋሙም አለን። ኢትዮጵያን የሚፈትኗት ኢትዮጵያን የማያውቋት ናቸው። ኢትዮጵያ ለሺ ዓመታት በነጻነት ኖረች ሲባል ትርጉሙን አይረዱትም ማለት ነው። ጠላት አጥታ አይደለም ሺ ዘመን በነጻነት የኖረችው። ፈተና ረስቷት አይደለም የነጻነት ቀንዲሏ ሳይጠፋ እስከ ዛሬ ያለው። ኃያላን ራርተውላት አይደለም ከከፍታዋ ያልወረደችው። ሁሉንም እንደ አመጣጣቸው አሸንፋ ብቻ ነው። ታሪካችንን ሳያውቁ የሚገጥሙንን ታሪካችንን ዐውቀን እንጠብቃቸዋለን። ለወዳጃችን ወተት፣ ለጠላታችን ዕሬት መስጠት እንችልበታለን። ከቶም ኢትዮጵያ የሚለው ስም ከማሸነፍ እንጂ ከመሸነፍ ጋራ ተጠርቶ አያውቅም። ከነጻነት እንጂ ከባርነት ጋራ ዝምድና የለውም። ኢትዮጵያ ተፈትና ታውቃለች። ተሸንፋ ግን አታውቅም። ቀጥና ታውቃለች፤ ተበጥሳ ግን አታውቅም። የዘመመች መስላ ታውቃለች፤ ወድቃ ግን አታውቅም። ይህ አዲሱ ዓመት ለ30 ዓመታት ኢትዮጵያን የተጣባትን ፈተና የምንገላገልበት፣ አዲስ መንግሥት የምንመሠርትበት፣ ከደረሰብን ፈተና የምናገግምበትና ፊታችንን ወደ ኢትዮጵያ ብልጽግና የምናዞርበት እንደሚሆን እምነቴ ነው። አዲሱ ዓመት ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችን የሚጸናበት፣ ዴሞክራሲያዊ ዕሴቶቻችን የሚጎለብቱበት፣ የጀመርነው ሪፎርም መልክ የሚይዝበት